የፌደራል መንግስት የድጋፍና ክትትል ቡድን በሶማሊ ክልል ያደረጉትን የምልከታ ሪፖርት ለክልሉ መንግስት አቀረበ

የመጋቢት 14 /2016 ዓ.ም(ኢ.ሚ) በኢፌዲሪ የግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ የተመራዉ የድጋፍና ክትትል ቡድን በሶማሊ ክልል ዞኖችና ወረዳዎች ያካሄዱት የአገልግሎት አሰጣጥ እና የተለያዩ የልማት ፕሮጀክቶች የምልከታ ሪፖርት ለክልሉ መንግስት አቅርቧል።

በሶማሊ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፋ ሙሁመድ እና በግብርና ሚኒስትሩ ዶ/ር ግርማ አመንቴ ሰብሳቢነት በተካሄደዉ መድረኩ ላይ የክልሉ ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኢብራሂም ኡስማንን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ የተለያዩ የቢሮ ሀላፊዎች የፌደራል መንግስት የድጋፍና ክትትል ቡድን አባላት ያቀረቡትን የምልከታ ሪፖርት አዳምጠዋል ።

የድጋፍና ክትትል ቡድኑ በክልሉ ዞኖችና ወረዳዎች በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ የሚታዩ ክፍተቶችን ለማሻሻል ከሚመለከታቸዉ የፌደራል መንግስት አካላት ጋር በመነጋገር መፍትሄ ለመስጠት በትኩረት እንደሚሰራ ተገልጿል ።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post