የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የሳፋሪ ተሸከርካሪ የምርት ሂደትን ጎበኙ

መጋቢት18/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የሳፋሪ ተሽከርካሪ የምርት ሂደት ያለበትን ደረጃ ጎበኙ፡፡

በሀገር ደረጃ የአገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ እና ለሀገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ ለመስጠት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአውቶ ሞቲቪ ዘርፉ የሳፋሪ ተሸከርካሪዎችን ለማምረት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ይህም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስፋት፣ የተኪ ምርት ስትራቴጂን እውን በማድረግ ፣ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ፣ለዜጎች ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግቦችን በማሳካት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

የምርት ሂደቱን በተመለከተም አብዛኛው የሜካኒካል ስራዎች መሰራታቸው የተገለጸ ሲሆን በቀሪ ጊዜያት የምርቱን ጥራትና ደረጃ በጠበቀ መልኩ ማጠናቀቅ የሚያስችል ስራ እየተሰራ መሆኑ ተገልጿል፡፡

አምራቾች ኢንዱስትሪዎቹን እያጋጠማቸው ያሉ ተግዳሮቶችን ለመቅረፍም ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እንደሚሰራ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ጠቁመል፡፡

Share this Post