በተለያየ ዘርፍ ከተሰማሩ የቻይና አምራች ድርጅቶች ጋር የኢንዱስትሪ ምቹ ሁኔታዎችና በዘርፉ ያሉ ዕድሎች ላይ ያተኮረ ዉይይት ከኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ጋር አድርገዋል።

በተለይ ኢትዮጵያ በተፈጥሮ ሀብት የታደለች፣ የሰለጠነና ሊሰለጥን የሚችል የኢንዱስትሪ የሰዉ ሀይል ያላት፣ በመንግስትና በግል ዘርፉ የተገነቡ ኢንዱስትሪ ፓርኮች መኖራቸው፣ በመልካ ምድራዊ አቀማመጥና ምቹ የአየር ሁኔታ መኖሩንም አማካሪው ገልጸው በዘርፉ ፍላጎት ያላቸው ባለሀብቶች እንዲሰማሩ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Share this Post