ለአምራች ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች የኢንዱስትሪ የሀይል አጠቃቀም ስርዓትን ለማዘመን የሚያስችል ስልጠና ተሰጠ
መጋቢት19/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር ለአምራች ኢንዱስትሪ ባለሙያዎች የኢንዱስትሪ የሀይል አጠቃቀም ስርዓትን ለማዘመን የሚያስችል ስልጠና ሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዋና ዓላማ በአምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የሚስተዋለውን የሀይል አጠቃቀም ችግር በመቅረፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ የሚሰተዋለውን የሀይል ብክነት ለመቀነስ የተያዘውን ግብ ማሳካት እንደሆነ ተገልጿ፡፡
የአምራች ኢንዱስትሪ የሀይል አጠቃቀም ስርዓትን ማዘመን የአካባቢ ብክለትን ከማስቀረቱ በላይ፣በየጊዜው የሚጨምረውን የህዝብ ቁጥር፣ኢኮኖሚያዊ ዕድገት፣የኢንዱስትሪዎችንና የከተሞችን መስፋፋት ተከትሎ የሚመጣውን ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት ለማርካት የላቀ አስተዋጽኦ እንዳለው የስልጠናው ተሳታፊዎች ተናግረዋል፡፡
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት