የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከጃፓን አምባሳደር ጋር በአምራች ኢንዱስትሪ እና ተያያዥ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ውይይት አደረጉ

መጋቢት19/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂርኖር ጋር በአምራች ኢንዱስትሪ እና እንደ ሀገር ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

በአምራች ኢንዱስትሪ ፖሊሲ፣ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች፣ የምርምር ማዕከላትን ማሳደግ እና በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ዙሪያ ተወያይተዋል::

በውይይታቸውም መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ለአብነትም የተዘጋጀው የኢንዱትሪ ፖሊሲ፣ እየተወሰዱ ያሉ ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች እና ያሉ የኢንቨስመንት ምቹ ሁኑታዎችን አንስተዋል፡፡

በአምራች ኢንዱትሪው ዘርፍ በርካታ ዕድሎችና ምቹ ሁኔታዎች እንዳሉ ገለጻ ያደረጉት ሚኒስትሩ የጃፓን ባለሃብቶች እንደ ሀገር ባሉ የኢንቨስትመንት አማራጮች እና ምቹ ሁኔታዎች ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በኢትዮጵያ ያሉ የኢንቨስትመንት እንቅስቀሴዎችን ለመደገፍ ፍላጎቱ እንዳላቸው የገለጹት የጃፓን አምባሳደር ሺባታ ሂርኖር የምርምር ማዕከላትን ለማጎልበት ፣እንደ ሀገር የተገነባውን የካይዘን የልዕቀት ማዕከልንና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የመደገፍ እና የኢትዮጵያን ኢንቨስትመንት አማራጮችን የማስተዋወቅ ፍላጎት እንዳላቸው ጠቁመዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post