የሕዳሴ ግድብ የኢትዮጵያውያን የጋራ ውጤት፣ የወል እውነት፣ የዚህ ትውልድ ደማቅ አሻራ፣ ለቀጣይ የልማት ሥራዎች መንደርደሪያ ዓቅም ነው::

ታላቁ የኢትዮጵያ ሕዳሴ ግድብ በዓባይ ወንዝ ላይ ለዘመናት ለነበረው የሕዝብ ቁጭት ምላሽ የሰጠ፣ የሉዓላዊነት መገለጫ እና የልማታችን ብርሃን በመኾን ከመጋቢት 24 ቀን 2003 ዓ.ም ጀምሮ ባለፉት 12 ዓመታት ለግድቡ ግንባታ ሁሉም ኢትዮጵያውያን ያለ ልዩነት በጉልበት፣ በእውቀት፣ በተፋሰስ ልማት ጥበቃ ሥራ፣ በፋይናንስ እና በፐብሊክ ዲፕሎማሲ የዜግነት ድርሻቸውን ሲወጡ ቆይተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ለዘመናት በዓባይ ወንዝ ላይ የማልማት ተስፋን ወደ ተግባር የመቀየር ጉልህ ተሞክሮ የታየበት፣ ኢትየጵያውያን ተፈጥሮ የለገሰቻቸውን ሀብቶች ተጠቅመው መልማት እንደሚችሉ በተጨባጭ ያሳየ፣ የኅብረ ብሔራዊነት እና ሀገራዊ አንድነት አርማ ነው፡፡

በየጊዜው ዓላማችንን እያስጨነቀ የመጣውን የአየር ንብረት ለውጥ ለመከላከል ታዳሽ የኃይል ምንጭ መጠቀም ግዴታ በኾነበት ዘመን የሕዳሴ ግድቡ ታዳሽ ኃይል ለጎረቤት ሀገሮች ጭምር ለማቅረብ ትልቅ መፍትሄ ይዞ የመጣ ፕሮጀክት ነው፡፡

በመሆኑም ሁሉም ኢትዮጵያውያ ተረባርበው በአንጡራ ሀብታቸውና በላባቸው የገነቡት ይህ ግድብ ከኢትዮጵያም አልፎ ለጎረቤት እና ቀጠናው አገሮች ፈርጀ ብዙ ተስፋን ይዟል፡፡

የሕዳሴ ግድቡን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ የተሳተፈው የዚህ ዘመን ትውልድ ለኢኮኖሚያዊና ማኅበረዊ ልማቶች መሠረት ከመጣል ባለፈ በኅብረት ሕያው አሻራውን አኑሯል ብሎ መውሰድ ይቻላል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post