በአምራች ኢንዱስትሪዎች የህፃናት ማቆያ ማዕከላት መኖር ለኢንዱስትሪው ዕድገት ከፍተኛ አስተዋጽኦ አለው (አቶ ሀሰን መሐመድ)

መጋቢት25/2016 ዓ.ም በይርጋለም ጋርመንት እና ኢትዮኢምፓክት አምራች ኢንዱስትሪዎች ውስጥ የተገነቡ የህፃናት ማቆያ ማዕከላት የምረቃ ስነ-ስርዓት ተካሂዷል፡፡

የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር ደኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ በአምራች ኢንዱስትሪዎች የህፃናት ማቆያ ማዕከላት መኖር ለሴት ሰራተኞች ምቹ የስራ ከባቢ ከመፍጠር ባሻገር ባለሙያዎቹ ሙሉ አቅማቸውን ተጠቅመው እንዲሰሩ በማድረግ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ፋይዳው የጎላ እንዲሆን ያደርገዋል ብለዋል፡፡

አቶ ሀሰን ሙሀመድ አክለውም በኢንዱስትሪው ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ሰራተኞችን አቅም ከማጎልበትና ምቹ የስራ ሁኔታን ከመፍጠር አኳያ ሚንስቴር መስሪያ ቤቱ የሚያደርገውን ድጋፍ አጠንክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post