ለኢንዱትሪያላዜሽን እድገት የቻይና መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል ተገለጸ

አዲስ አበባ 27/7/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከቻይናው አምባሳደር ዛኦ ዚዩዋን ጋር የሁለቱን አገራት ትስስር በሚያጠናክሩ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

ቅባቱ የወጣለት የአኩሪ አተር ምርት ኤከስፖርት፣ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎችና የትምህርት እድሎች ፣ከሶስትዮሽ የግንኙነት አግባብ ውስጥ በተለይም የልዕቀት ማዕከላት ግንባታ ላይ ያተኮረ ውይይት አድርገዋል፡፡

መንግስት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር እና ኢንዱስትሪያላዜሽን ለማምጣት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትኩረት ሰጥቶ እየተንቀሳቀሰ ነው ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል የቻይና መንግስት ለአምራች ኢንዱትሪ ዘርፍ እያደረገ ላለው አስተዋጽኦ ምስጋናቸውን አቅርበው ድጋፋቸውን አጠናክረው እንዲቀጥሉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሁለቱ አገራት መካከል ጠንካራ ግንኙነት መኖሩን ያነሱት የቻይናው አምባሳደር ዛኦ ዚዩዋን የሁለትዮሽ ግንኙነቱን ይበልጥ ለማጠናከር በተለይም በኢትዮጵያ ኢንዱትሪያላያዜሽን እድገት ላይ የቻይና መንግስት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post