በም/ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪን ጎበኙ

መጋቢት 28/2016ዓ.ም(ኢ.ሚ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።

በሀገር ደረጃ የአገር ውስጥ አምራቾችን ለማበረታታ እና ለሀገር ውስጥ ምርቶች ቅድሚያ ለመስጠት በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት በአውቶ ሞቲቪ ዘርፉ የሳፋሪ ተሸከርካሪዎችን ለማምረት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ይህም የቴክኖሎጂ ሽግግርን በማስፋት፣ የተኪ ምርት ስትራቴጂን እውን በማድረግ ፣ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ፣ለዜጎች ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር እና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ግቦችን በማሳካት ረገድ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገልጿል፡፡

በጉብኝቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል፣ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post