ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ፣ለዜጎች ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አምራች ኢንዱስትሪ ትልቅ ሚና እንዳለው ተገለፀ።

መጋቢት 28/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ) በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ሃላፊዎች ልዑክ የሳፋሪ ተሸከርካሪዎችን ማምረቻ ኢንዱስትሪዎችን የሥራ እንቅስቃሴን ጎብኝቷል።

በጉብኝቱ ወቅት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በሙከራ ማምረት ሂደት አምራች ኢንዱስትሪዎቹ በስራ ላይ እያጋጠሙ ያሉ ተግዳሮቶችን በቅርበት ለይቶ በተፈለገው የጥራት ደረጃ ምርቶቹ እንዲመረቱ ለማድረግ እና ለመደገፍ በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶ እየተሰራ ነው ብለዎል።

በተለይም በመንግስት ትኩረት ተሰጥቶ ከሚሰሩ ዘርፎች መካከል የአምራች ኢንዱስትሪና ቱሪዝም መሆናቸውን ያነሱት ሚኒስትሩ ዘርፋን እርስ በርስ በማደጋገፍ የቱሪዝምን የትራንስፖርት አቅርቦት ለማዘመንና ለማሻሻል በተመረጡ አምራች ኢንዱስትሪዎች ላይ የሳፋሪ ተሸከርካሪዎችን የሙከራ ምርት ሂደቱ ውጤታማ መሆኑን አስረድተዋል ።

በቀጣይ የምርቱን ጥራት በማስጠበቅ የተሻለውን ዲዛይን በመምረጥ በሌሎች ኢንዲስትሪዎች በማስፍፍት የምርቱን መጠን በማሳደግ ለወጪ ገበያ ለማቅረብ እንደሚሰራም ገልፀዋል

ለቱሪዝም ዘርፉ ምቹ ሁኔታዎችን በመፍጠር ፣ለዜጎች ዘላቂ የስራ እድል በመፍጠር ረገድ አምራች ኢንዱስትሪ ትልቅ ሚና እንዳለው ሚኒስትሩ አስረድተዋል ፡፡

የኤሌክትሪክ ኃይል የሚያገለግሉ ትልልቅ ምሶሶዎችና ከፍተኛ ኃይል ያላቸውን የኤሌክትሪክ ኃይል ማስተላለፊያ ገመድ በማምረት እንደ አገር ከውጪ የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለማስቀረት የሚደረገው ጥረት በጉብኝቱ መመልከታቸዉን ገልፀዋል ።

በጉብኝቱ የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)፣ የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ ጨምሮ ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ሃላፊዎች ተሳትፈዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post