ለቱሪዝም ዘርፍ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ስኬታማ ሥራ እየተከናወነ ነው (አቶ ተመስገን ጥሩነህ)

መጋቢት 29/2016(ኢ.ሚ) ለቱሪዝም ዘርፍ የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ስኬታማ ሥራ እየተከናወነ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ መንግሥት ተኪ ምርቶችን ለማስፋት ያስቀመጠው አቅጣጫ ለማስፈጸም በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ በተለይም ለአምራች ኢንዱስትሪው የሚደረገው ዘርፈ ብዙ ድጋፎች ተኪ ምርትን ለመተካት መሰረት እየጣለ መሆኑን ነው ያስረዱት።

ከዚህ አንጻር ለቱሪስት እንቅስቃሴ አጋዥ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ ለማሟላት ፋብሪካዎች እያደረጉት የሚገኘው ጥረትም የሚበረታታ መሆኑን ለኢዜአ ተናግረዋል።

በቱሪዝም መስክ ያለውን አቅም ጥቅም ላይ ለማዋል እንቅፋት የሆነውን የተሽከርካሪ እጥረት በሀገር ውስጥ ምርት ለማሟላት ስኬታማ ሥራ እየተሰራ መሆኑን ጠቁመዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ የማምረቻ ኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸዉ ይታወሳል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post