የሀገር ዉስጥ ምርትን መጠቀም አርበኝነት ነዉ /ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር)/

መጋቢት 29/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ)የትራንስፖርትና ሎጂስቲክስ ሚኒስትር ዓለሙ ስሜ (ዶ/ር) በኢትዮጵያ ታምርት ተነሳሽነት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ስኬት እያስመዘገበ ነው ያሉት ሚንስትሩ የሀገር ዉስጥ ምርትን መጠቀም አርበኝነት እንደሆነም ገልጸዎል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ለቱሪዝም ዘርፍ የሚውሉ ተሽከርካሪዎች በሀገር ውስጥ እንዲመረቱ ያስቀመጡት አቅጣጫም በአጭር ጊዜ ውጤት አስገኝቷልም ብለዎል።

ለኢንዱስትሪ ዘርፍ እየተደረገ የሚገኘው ድጋፍም በራስ አቅም የአገር ውስጥ ምርትን አምርቶ መጠቀም እንደሚያስችል ስኬት የተገኘበት መሆኑን አንስተዎል።

የኢትዮ-ኢንጂነሪንግ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አምባሳደር ሱሌማን ደደፎ፤ የቢሾፍቱ አውቶሞቲቭ ማምረቻ ኢንዱስትሪ ከከባድ እስከ ቀላል የህዝብ፣ ወታደራዊና ለግንባታ አገልግሎት የሚውሉ ተሽከርካሪዎችን አምርቶ እያቀረበ መሆኑን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የአርሶ አደሩን የግብርና ምርታማነት የሚያግዙ ተሽከርካሪዎችን በማምረት ሂደት ላይ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ የተመራ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ልዑክ ቡድን የማምረቻ ኢንዱስትሪ የሥራ እንቅስቃሴዎችን ተዘዋውረው መጎብኘታቸዉ ይታወሳል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post