የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ከአፍሪካ ህብረት ንግድና ኢንዱስትሪ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጋር ተወያዩ።

መጋቢት 30/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢፌድሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚንስትር አቶ መላኩ አለበል ከአፍሪካ ንግድና ኢንዱስትሪ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሚስተር አልበርት ሙቻንጋ ጋር አብሮ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡

የውይይቱ ዋና ዓላማ ግብርናን እና ኢንዱስትሪን ተመጋጋቢ አድርጎ በመስራት ኢንዱስትሪውን ለማዘመን የሚያስችሉ ስራዎች ላይ ያተኮረ ነበር፡፡

በአህጉር ደረጃ ተቀናጅቶ መስራቱ ጥሩ ተሞክሮዎችን ከመለዋወጥ ባሻገር ለአፍሪካ ኢንዱስትሪ ዕድገት ፋይዳው የጎላ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አብራርተዋል፡፡

ሚስተር ሙቻንጋ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የአፍሪካ ህብረት መቀመጫ እንደመሆኗ መጠን መስሪያቤታቸው የሀገሪቱን ኢንዱስትሪ ለመደገፍ አብሮ ለመስራት ፈቃደኛ መሆኑን በመግለፅ በቀጣይ የአፍሪካ ህብረት በሚያካሂደው የኢንዱስትሪ ሳምንት ዓውደ ርዕይ ኢትዮጵያ ተሳታፊ እንድትሆንና ክቡር ሚንስትሩም በመርሀ ግብሩ ተገኝተው ንግግር እንዲያደርጉ ጋብዘዎቸዎል።

Share this Post