የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የኢድ አልፈጥር በዓልን ምክንያት በማድረግ ድጋፍ አደረገ

ሚያዚያ1/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ፕርፎርማንስ ፕሮጀክት በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት አሚባራ ወረዳና በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሽንሌ ወረዳ ለሚገኙ የፕሮጀክቱ የሳይት ሰራተኞች እና ለአካባቢው ማህበረሰብ ድጋፍ አድረገ።

የፕሮጀክቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ዳዊት አለሙ ድጋፉ በሁለቱም ፕሮጀክት ሳይቶች ለሚገኙ ነዋሪዎች እና ሳይት ሰራተኞች የኢድ-አልፈጥርን በዓል ምክንያት በማድረግ የተደረገ ድጋፍ መሆኑን ገልፀዋል።

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የአርሶ አደሩን የእርሻ መሬት በመውረር የአካባቢውን ስነ ምህዳር በማዛባት የህብረተሰቡ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እያሳደረ ያለውን የፕሮሶፒስ ጁሊፍሎራ /መጤ አረም/ በዘመናዊ ማሽን ከአካባቢው በማጽዳት የእርሻ መሬቱን እንዲጠቀሙበት ከማድረጉም በላይ መጤ አረሙን ወደ አማራጭ የሃይል ምንጭነት እየቀየረ ይገኛል፡፡

የሲሚንቶ ፋብሪካዎች ለድንጋይ ከሰል የሚያወጡትን የውጪ ምንዛሬ ለመቀነስ መጤ አረሙን ወደ አማራጭ የሃይል ምንጭነት መቀየሩ ያመጣው ፋይዳ የጎላ መሆኑንም ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

አቶ ዳዊት አክለውም ድጋፉ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከህብረተሰቡ ጎን መሆኑን ለመግለፅና እንኳን ለኢድአልፈጥር በዓል አደረሳችሁ ለማለት እንደሆነ በመግለፅ ድጋፉ በተጠናከረ ሁኔታ እንደሚቀጥልም ገልፀዋል ።

Share this Post