የሚኒስትሮች ምክር ቤት የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ረቂቅ ፖሊሲ አፀደ

የሚኒስትሮች ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው 29ኛ መደበኛ ስብሰባ ውሳኔ ካስተላለፈባቸው ጉዳዮች አንዱ የጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ልማት ረቂቅ ፖሊሲ መሆኑ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

ፖሊሲው ለጥቃቅን፣ አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ምስረታ፣ እድገትና መስፋፋት ምቹ ሁኔታ በመፍጠር፣ ለዘርፉ የሚሰጡ ድጋፎች ፍላጎትን እና አቅምን ያገናዘቡ እንዲሆኑ በማድረግ፣ ኢመደበኛ የንግድ ስራዎችን በመደገፍ የዘርፉ ልማት አካታች እንዲሆን በማድረግ በኢኮኖሚው ላይ የሚኖረውን በጎ አስተዋፅዖ ከፍ ለማድረግ የሚያስችል ሆኖ ቀርቧል፡፡

ምክር ቤቱም በረቂቅ ፖሊሲው ላይ ከተወያያ በኋላ ግብዓቶችን በማከል በስራ ላይ እንዲውል በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post