ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሆነችበትን ምክንያቶች የሚያብራራ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
አዲስ አበባ 01/08/2016 ዓ.ም (ኢሚ) ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሆነችበትን ምክንያቶች በማጉላት በተተገበሩ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችና ሀገራዊ ማሻሻያዎች ላይ በማተኮር ባለሃብቱ ለምን ኢትዮጵያ ውስጥ ኢንቨስት እንደሚያደር ማብራሪያ ለመሥጠት ያለመ የፓናል ውይይት ተካሄደ፡፡
የፓናል ውይይቱ ኢትዮጵያ ተመራጭ የኢንቨስትመንት መዳረሻ የሆነችበትን ምክንያቶች በማጉላት በተተገበሩ አዳዲስ የኢንዱስትሪ ፖሊሲዎችና ሀገራዊ ማሻሻያዎች ላይ በማተኮር ክብርት ኮሚሽነር ወይዘሮ ሃና አርአያስላሴ የኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ኮሚሽን፣ ክቡር አምባሳደር ምስጋኑ አረጋ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ፣ አቶ ዘመዴነህ ንጋቱ ግሎባል ቼርማን ፌርፋክስ አፍሪካ ፈንድ ፣ አቶ አዲስ አለማየሁ የካዛና ቡድን ሊቀመንበር፣ ዶ/ር ተስፋቸው ታፈረ ቶኒ ብሌየር ኢንስቲትዩት የፖሊሲ ከፍተኛ አማካሪ፣ አቶ ደጀኔ ተዘራ የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ዳይሬክተርና ሚዩሚዩ ሚያዮ ባኦባብትሪስ ክሮስቦርደር ሰፕላይ ቼይን ዋና ስራ አስፈጻሚ ፣ ከዓለም ባንክ የግሉ ዘርፍ ከፍተኛ ባለሙያ በወ/ሮ ስንዱ ፋኑኤል አወያይነት ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች ና የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት የፓናል ውይይት ተካሄ ፡፡
በውይይቱም በተለያዩ የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ዘርፎች ለሚሰማሩ ባለሀብቶች ያለውን ዕድልና ማበረታቻ እና ምቹ የኢንቨስትመንት ሁኔታን ለመፍጠር አስተዋፅዖ ያበረከቱትን ቁልፍ የፖሊሲ አቅጣጫዎችን ተብራርቷል።
ቁልፍ ዘርፎችን ለውጭ ባለሃብቶች መከፈት፣ የንግድ ስራ ቀላልነት እና የባለሃብቶች ጥበቃ እርምጃዎችን የመሳሰሉ የቅርብ ጊዜ ማሻሻያዎችን በተመለከተ ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡
ኢንቨስትመንቶችን የሳቡ ልዩ ፖሊሲዎች፣ ባለሀብቶች ያጋጠሟቸውን ተግዳሮቶች እና የመንግስትና የግሉ ዘርፍ አጋርነት ኢንቨስትመንትን በማስተዋወቅ ረገድ ያለውን ሚና በተመለከተ ተሳታፊዎች ላነሷቸው ጥያቄዎች በተወያዮቹ ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል ፡፡
ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት