በኢትዮጵያ ያለው የኢንቨስትመንት እና የግሉ ዘርፍ የቢዝነስ ሁኔታ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም (ኢሚ) በኢትዮጵያ ያለው ባያለው የኢንቨስትመንት እና የግሉ ዘርፍ የቢዝነስ ሁኔታ ላይ በማተኮር የአምራች ኢንዱስትሪ ባለሀብቶች እና ቢዝነሶች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶችን በመፈተሽ ውይይት እየተደረገባቸው ነው።

በተለይም ከኢንቨስትመንት ማስተዋወቅ፣ ከንግድ ደንቦች እና ለግሉ ሴክተር ዕድገት ምቹ ሁኔታን በመፍጠርን በተመለከተ ውይይት ይደረግባቸዋል ።

በውይይቱ በኢትዮጵያ ስላሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ሰፊ ዳሰሳ የሚሰጥ ሲሆን ኢንቨስተሮችን የሚስቡ ወይም የሚያግዱ ሁኔታዎችን በማሳየት ተወያዮች እንደ የፋይናንስ አቅርቦት፤ የመሰረተ ልማት አቅርቦት፤ የሃገር ውስጥ ጥሬ እቃ አቅርቦት ላይ በማተኮር ሃሳባቸውን ያነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

Share this Post