የተረጋጋ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት ለአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነት አስፈላጊ ነው (አቶ ማሞ ምህረቱ የብሔራዊ ባንክ ገዥ)

አዲስ አበባ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 ላይ የግል ኢንቨስትመንት እና አስቻይ ሁኔታዎች በሚል ርዕሰ ጉዳይ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው።

ለአምራች ኢንዱስትሪዎች የፋይናንስ እና የመሠረተ ልማት አቅርቦቶችን በተመለከተ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች እና ተግዳሮቶች ላይ ትኩረቱን ባደረገው ውይይት ላይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ አቶ ማሞ ምህረቱ የተረጋጋ የፋይናንስ ሥርዓት መዘርጋት ለአምራች ኢንዱስትሪ ምርታማነት አስፈላጊ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያን ልማት ባንክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ዮሃንስ አያሌው በበኩላቸው በሀገራችን እያደገ የመጣው የምርት ፍላጎትን ለማሟላት የሀገር ውስጥ አምራቾችን አቅም ማሳደግ ያስፈልጋል ብለዋል።

ለዚህም የልማት ባንክ ብድር በቅድሚያ ማቅረብ ብቻ ሳይሆን በአነስተኛ ወለድም በመስጠት ለዘርፉ ትኩረት ተሰጥቶት እየሠራ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post