የአምራች ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት ለማርካት ስራዎች እየተሰሩ ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም(ኢሚ) በሀገር አቀፍ ደረጃ የተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ኢንዱስትሪዎች መነቃቃታቸውና ወደስራ መግባታቸውን ተከትሎ የተጠረውን የሀይል ከፍተኛ የኃይል ፈላጎት ለማሟላት መጠነ ሰፊ ስራዎች እየተሰሩ እንደሆነ የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢንጅነር አሸብር ባልቻ ገልፀዋል።

ኢንዱስትሪና ሀይል ሊነጣጠሉ የማይችሉ ጥብቅ ቁርኝት ያላቸው ዘርፎች መሆናቸውን የገለጹት ዋና ስራ አስፈፃሚው የአምራች ኢንዱስትሪውን ከፍተኛ የሀይል ፍላጎት ለማርካት የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ በችግሮች ዙሪያ ተቀራርቦ ለመነጋገርና መፍትሔ በመስጠት ረገድ ጉልህ ሚና እየተጫወተ መሆኑን ጠቁመዋል።

ኢንጅነሩ አክለውም አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚያመርቷቸው ምርቶች ለሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች በግብዓትነት ስለሚያገለግሉና ኢትዮጵያ ያላትን ምቹ የተፈጥሮ ፀጋዎች ግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ባለሀብቶች በሀይል ማመንጫ ፕሮጀክቶች ቢሳተፉ አዋጭ መሆኑን ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post