የአምራች ኢንዱስትሪውን የገንዘብ አቅርቦት ችግር ለመፍታት አዳዲስ የፖሊሲ ማሻሻያዎች እየተደረጉ ነው

አዲስ አበባ ግንቦት 03/2016 ዓ.ም (ኢሚ)ቀደም ሲል በአምራች ኢንዱስትሪዎች በኩል እንደ ማነቆ ሲጠቀስ የነበረውን የብድር አቅርቦት ችግር ለመቅረፍ መንግስት አዳዲስ የፖሊሲ ማሻሻያዎችን ያደረገ መሆኑን የብሔራዊ ባንክ ገዥ ክቡር አቶ ማሞ ምህረቱ ገልጸዋል።

ባለፉት ዘጠኝ ወራት የዋጋ ንረትንና ግሽበትን ከማሻሻል አንፃር የገንዘብ ተቋማት በተቻለ መጠን ለአምራች ኢንዱስትሪው እንዲያተኩሩ ተደርጓል ያሉት ዋና ገዥው የጥቃቅንና አነስተኛ ኢንዱስትሪ ባለቤቶች አቅማቸውን እንዲያጎለብቱ ተጨማሪ ብድር የሚያገኙበትን ስርዓት የመዘርጋት ስራም እንደሚሰራ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post