ጥናትና ምርምር ለተሻለ አቅም ግንባታ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለውን ፋይዳ ትኩረት ያደረገ የፓናል ውይይት እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ 04/08/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ፣ የአቅም ግንባታ እና የክህሎት ልማት በኢትዮጵያ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ያለውን ፋይዳ ትኩረት በማድረግ ፈጠራን፣ ምርታማነትን ለማሳደግ እና የኢንዱስትሪ ፍላጎቶችን ለማሟላት የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት መሰራት ያለባቸው ስራዎችን በተመለከተ ውይይት ይደረጋል ።

የኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ሁኔታ፣ የምርምር አቅምን በመገንባት ላይ ያሉ ተግዳሮቶችን እና የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት ስልቶችን በመቅረፍ የኢትዮጵያን የኢንዱስትሪ ልማት ጥረቶችን ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር ተግባራዊ ሊሆኑ የሚችሉ ጠቃሚ ሀሳቦች በውይይቱ ይነሳሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ተወያዮች ዕውቀታቸውን ያካፍላሉ፣ የተሳካ የኢንዱስትሪ ምርምር እና ልማት ምሳሌዎችን እና የአቅም ግንባታ ውጥኖችን በማጉላት የክህሎት ልማት ፕሮግራሞች ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ያለውን ፋይዳ አጉልቶ በማሳየት የሚመለከተው ሁሉ ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራ ማድረግ የሚያስችል ውይይት ያደርጋሉ ።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post