የጥናትና ምርምር ስራዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው(ክቡር አቶ መላኩ አለበል)

በኢትጵያ ታምርት 2016 ኤክስፖ ጥናትና ምርምር ለተሻለ አቅም ግንባታ በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ነው ::

የጥናትና ምርምር ስራዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉን በማጠናከር ረገድ ትልቅ ሚና አላቸው ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በአለም ላይ የአምራች ኢንዱስትሪው እያደገ መምጣቱንና አብዛኛው ወደ ሰው ሰራሽ አስተውሎት እየተሸጋገረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ጊዜውን የዋጀ የጥናትና ምርምር ስራዎች መስራት ያስፈልጋል ሲሉ ጠቁመዋል::

የሰው ሰራሽ አስተውሎት 40 በመቶ የስራ አድል እንደሚቀንስ የአለም አቀፍ የገንዘብ ፈንድ (IMF) ትንበያ ያመላክታል ያሉት ሚኒስትሩ ይህንንና መሰል ችግሮችን ለመፍታት መሻሻል የሚገባቸውን ቴክኖሎጂዎችን ማሻሻል፣ ለአዳዲስ ቴክሎጂ ፈጠራዎች ትኩረት መስጠት፣ በትምህርት ታቋማት ውስጥ አዳዲስ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ማሳደግና ቅንጅታዊ አሰራሮችን በመፍጠር ለዘርፉ እድገትና ተወዳዳሪነት ሁሉም የኩሉን ድርሻ እንዲወጣ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post