ኢኮኖሚውንናየአምራች ኢንዱስትሪውን ለመደገፍ በእውቀት የዳበረ ትውልድ የማፍራት ስራ እየተሰራ ነው

ኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፓ "ጥናትና ምርምር ለተሻለ አቅም ግንባታ" የፓናል ውይይት የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሀኑ ነጋ (ፕ/ሮ) እንደገለፁት የሀገሪቱን ኢኮኖሚና አምራች ኢንዱስትሪው ለመደገፍ በእውቀትና ክህሎት የዳበረ ትውልድ የማፍራት ስራ እየተሰራ ነው ።

በትምህርት ስርዓት ማሻሻያው የትምህርት ተቋማት የእውቀት ማዕከል እንዲሆኑና የሀገሪቱን ኢኮኖሚ እንዲደግፉ እየተሰራ ነው ብለዋል።

የትምህርት ስርዓት ማሻሻያው አምራች ኢንዱስትሪው ከጥናትና ምርምር ስራው ጋር ትስስር እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰሩት ጥናትና ምርምር ከኢንዱስትሪዎች ጋር ትስስር ያለው እንዲሆን ግዴታ መጣሉን ገልጸው፤ ኢንዱስትሪዎችም ለጥናትና ምርምር በጀት መመደብና ተማሪዎች በተግባር የሚማሩበትን ምቹ ሁኔታን ሊፈጥሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

የስራና ክህሎት ሚኒስትር ደኤታ ተሻለ በሬቻ (ዶ/ር) በበኩላቸው በቴክኒክና ሙያ የሚያልፉ ዜጎች ክህሎት መርና ለአምራች ኢንዱስትሪ ገበያው ተፈላጊ የሆነ ስልጠናን እንዲያገኙ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚፈልጉትን የሰው ሀይል የማፍራት ስራ በልዩ ትኩረት እየተሰራ ስለመሆኑም ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post