የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፓ መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ ትኩረት ለመስጠቱ ዋና ማሳያ ነው (የተከበሩ አቶ አደም ፋራህ)

አዲስ አበባ ግንቦት 05/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የዲሞክራሲ ስርዓት ማዕከል ኃላፊ አቶ አደም ፋራህ የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፓ መዘጋጀት መንግስት ለዘርፉ ከፍተኛ ትኩረት መስጠቱን ያሳያል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ታምርት 2016 ኤክስፖን በመጎብኘት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት አቶ አደም የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በሀገረ አቀፍ ደረጃ ከተጀመረ ወዲህ ኢንዱስትሪዎች ከመነቃቃታቸው ጋር ተያይዞ የውስጥና የውጭ ኢንቨስተሮች ለዘርፉ ያላቸውን ግንዛቤ ማደጉን ገልፀዋል ።

በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ምክንያት ኢንዱስትሪዎች የእርስበርስ የገበያ ትስስር መፍጠር መቻላቸውንም ተናግረዋል ።

በመጨረሻም የዲሞክራሲ ስርዓት ማዕከል ኃላፊው አቶ አደም ፋራህ ንቅናቄው ግቡን ይመታ ዘንድ ሁሉም ባለድርሻ አካል የበኩሉን አስተዋፅኦ እንዲያደርግና በሀገር ውስጥ ምርት የመጠቀም ልምዳችን መስተካከል እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post