የአምራች ኢንዱስትሪውን በመደገፍ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግሩን ዕውን ለማድረግ በመንግስት በኩሉ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክው ይቀጥላሉ (ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ )

አዲስ አበባ ግንቦት 05/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ 2016 ማጠቃላያ መርሃ ግብር የኢፌዲሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩንህ፣ ጥሪ ያተደረገላቸው ከፍተኛ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች የአምራች ኢንዱስትሪ ባለቤቶች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ተካሄደ።

በማጠቃለያ መርሃ ግብሩ የንቅናቄው ዋና አላማ የአምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነት ለማሳደግ እንደሀገር ያሉንን የልማት እድሎች መጠቀም እና የዘርፉን ተግዳሮቶች በቅንጅት መፍታት ነው ያሉት የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ተመስገን ጥሩነህ እንዚህን አላማዎች በመያዝ በዘርፉ ኢኮኖሚያዊ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት በመንግስት በኩሉ የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል።

ንቅናቄው መንግስት ለዘርፉ የሰጠው ትኩረት ለለውጡ ማሳያ ነው ሆኖም እንደ ሀገር ካላው የመልማትት ፍላጎትና አምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ማነቆ አኳያ ቀጣይነት ያለው ክትትልና ድጋፍ አስፈላጊ ነው ሲሉ አክልዋል።

የቀጣይ አቅጣጫዎችን በተመለከተም ንቅናቄውን በማጎልበት ሊያሳካቸው ያስቀመጣቸውን አላማዎች በአግባቡ በመተግበር ተጨባጭ ውጤቶችን ማረጋገጥ፣ የአምራች ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አምቅ አጠቃቀም ተግዳሮቶችን ዘላቂና ታቋማዊ በሆነ አግባብ በቅንጅት መፍታት፣ የአምራች ኢንዱሰትሪውን የሀገር ውስጥ የገበያ ድርሻ በተኪ ምርት ስትራቴጂ ማሳደግ የሚሉት ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ ካነሱሱዋቸው የቀጣይ አቅጣጫዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post