የአውሮፓ ህብረትና አጋሮቹ ግጭት በነበረቻቸው አካባቢዎች የሚገኙ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚደገፉበትን ፕሮግራም ይፋ አደረጉ
ግንቦት 7/2016ዓ.ም(ኢ.ሚ)የአውሮፓ ህብረት እና አጋሮቹ የአካባቢን ኢኮኖሚ ወደነበረበት ለመመለስ እና አነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መልሶ ማቋቋም የሚያሰችላቸውን ፕሮግራም ይፋ አድርገዎል።
ፕሮግራሙ በሰሜን ኢትዮጵያ ከግጭት በኋላ ያሉ አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱትሪዎችን በተሻለ የፋይናንስ አቅርቦት ለመደገፍ ዓላማ ያደረገ ሲሆን ይህም በግጭቱ ጉዳት የደረሰባቸውን አምራች ኢንዱስሪችና በግብርና ማቀነባበር ዘርፍ ላይ የተሰማሩትን በመደገፍ ወደ ምርትና ምራታማነታቸው ለመመለሰ ያለመ ነው፡፡
የአውሮፓ ህብረት ፣ ኔዘርላንድስ እና ጀርመን ቀጣይነት ባለው መልኩ ወሳኝ በሆኑ ዘርፎች እያደረጉ ያሉትን ድጋፍ ያሳያል ያሉት የኢንዱስትሪ ሚኒስተር ዴኤታ አቶ ሀሰን ሙሀመድ በሴቶችና ወጣቶች የስራ እድል ፈጠራ ላይ ልዩ ጠቀሜታ አለው ሲሉ አክለዋል።
አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎችን መደገፍ ማህበራዊ ትስስርን የማጠናከር፣ ኢኮኖሚ እንዲያገግም የማድረግ እና ሰላምን በማስፈን ረገድ ትልቅ ሚና አለው ሲሉ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ሮላንድ ኮቢያ ገልጸዋል፡፡