የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አህጉሪቱን በኢንዱስትሪና በንግድ ለማሳደግ እንዲሁም የኢኮኖሚ ውህደትን ለማፋጠን የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል አለባቸው(አቶ መላኩ አለበል)

ኢትዮጵያ በንግድ፣ ቱሪዝም፣ ኢንዱስትሪያልላይዜሽን እና የማዕድን ሀብት ልማት የተነደፉትን የህብረት ጅምሮች እንደምትደግፍ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በ 4ኛው የአፍሪካ ህብረት ልዩ የቴክኒክ ኮሚቴ ስብሰባ ላይ ገለጹ፡፡

በአፍሪካ ህብረት አጀንዳ 2063 እና በዘላቂ ልማት ግቦች (SDGs) ውስጥ የተካተቱትን ዕቅዶች ለማሳካት ለኢንዱስትሪያላይዜሽን እና የንግድ ተወዳዳሪነት የቴክኒክ ኮሚቴው ትኩረት ሊሰጠው ይገባል ያሉት አቶ መላኩ የአፍሪካ ህብረት አባል ሀገራት አህጉሪቱን በኢንዱስትሪና በንግድ ለማሳደግ፣ እና የኢኮኖሚ ውህደትን ለማፋጠን የሚያደርጉትን ጥረት አጠናክረው መቀጠል አለባቸው ብለን እናምናለን ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ኢንዱስትሪያላይዜሽንን ለማፋጠን እና ኢኮኖሚን ለመቀየር አህጉሪቱ አስፈላጊ ግብአቶችን ማሰባሰብ አለባት ያሉት ሚኒስትሩ የማዕድን ሀብቶቻችን እና የቱሪስት መስህብ ቦታዎች በአህጉሪቱ ኢንደስትሪየላይዜሽን እውን ለማድረግ አስፈላጊ ሀብቶችን እንድታፈራ ያስችላታል ለዚህም ራዕያችንን ወደ ተግባር ምዕራፍ በመተርጎም ረገድ የአመራር ሚና ወሳኝ ነው ሲሉ አክለዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአስር አመት ኢኮኖሚ ልማት እቅድ (2021-2030) ቁልፍ ከሆኑ የትኩረት አቅጣጫዎች አንዱ ነው ኢንዱስትሪያላዜሽን ማምጣት ነው ያሉት አቶ መላኩ ለዚህም አስፈላጊውን የፖሊሲ ዝግጅት በማድረግ አመርቂ ውጤት ማስገኘቷን፣ጠንካራ የጨርቃጨርቅ፣ቆዳና ቆዳ ውጤቶች፣ ምግብና መጠጥ ኢንዱትሪዎች መገንባት መቻላቸው፣በርካታ የኢንዱስትሪ ፓርኮችን እና ነፃ የኢኮኖሚ ዞኖችን አስፈላጊ በሆኑ መገልገያዎችን እና የአንድ የመስኮት አገልግሎት መዘጋጀቱን፣ከውጪ ወደ አገር ውስጥ የሚገቡ ምርቶችን በአገር በቀል ምርቶች ለመተካት የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መጀመሩን አንስተዋል፡፡

ስብሰባው በአፍሪካ የንግድ ተወዳዳሪነት ፣ኢንዱስትሪላይዜሽን ፣ቱሪዝም ፣ የማዕድን ሀብት ልማት እና ሌሎች ወቅታዊ አጀንዳዎች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ነው፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post