የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መልካምና ተስፋ ሰጭ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ ነው (ዶ/ር ፈቃዱ መንግስቱ )

ግንቦት 15/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) በአምራች ኢንዱስትሪው ለዘርፉ መንግስት በሰጠው ትኩረት ከአምስቱ የኢኮኖሚ ዘርፎች አንዱ ነው ያሉት የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ምክትል ሰብሳቢው የተከበሩ ዶ/ር ፈቃዱ መንግስቱ በእቅድ ግምገማችን የመስክና የዴስክ የክትትልና ጉብኝት ሂደቶች እንዳረጋገጥነው የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር መልካምና ተስፋ ሰጭ ስኬቶችን በማስመዝገብ ላይ መሆኑን ቋሚ ኮሚቴው ማረጋገጥ መቻሉን የቋሚ ኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ ገልፀዋል፡፡

የተከበሩ ዶ/ር ፈቃዱ ኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ የተዘጉ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ እንዲመለሱ ከላይ እስከ ታች ያለው መዋቅር በቅንጅትና በመናበብ ውጤታማ ስራ በመስራት የዘርፉን ሀገራዊ ወሳኝነት በማረጋገጥ ረገድ ትልቅ አስተዋፅኦ እያበረከተ ነው ብለዋል፡፡

የንቅናቄው ስትሪንግ ኮሚቴዎች በየዘርፉ ተዋቅረው የጋራ እቅድ በማዘጋጀት በየጊዜው እየገመገሙ በመስራት ለንቅናቄው ውጤታማነት ያለውን አስተዋፀኦ ከፍተኛ ስለመሆኑም ገልፀዋል፡፡

የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ የሚለወጠው ከውጭ በሚገቡ ምርቶች አይደለም ያሉት የተከበሩ ዶ/ር ፈቃዱ የሀገራችንን ዕድገት እውን ለማደረግና ለዜጎች ዘላቂና አስተማማኝ የስራ ዕድል ለመፍጠር የሀገር ውስጥ ተኪ ምርቶች ላይ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት እንደሚገባ ገልጸው የተኪ ምርቶች ስትራቴጅ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱንም አንስተዋል፡፡

ሁሉም ዜጋ የሀገራችን ኢኮኖሚ ከፍ እንዲል የመፈለጋችንን ያህል በሀገራችን ምርት የመጠቀሙ ልማድ ዝቅተኛ መሆኑን የጠቀሱት ምክትል ሰብሳቢው በሀገራችን ምርት በኩራት የመጠቀምና ምርቱን የማስተዋወቅ ስራ መስራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post