የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታ ላይ ተፈራረመ።

ሐምሌ 12/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ) ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር በጋራ ለመስራት የሚያስችለውን ስምምነት ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር በኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታ ላይ ያተኮረ ስምምነት ተፈረመ።

ስምምነቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እና የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ በሚያስችሉ በኢንዱስትሪ አመራር አቅም ግንባታና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ተፈራርመዋል።

ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል እንደገለፁት ስምምነቱ በአምራች ኢንዱስትሪ አመራርና ሠራተኞች አቅም ልማት ፕሮግራም፣ የላቀ አፈፃፀም ያሳዩ የዘርፉ ተዋንያንን የማትጊያ ሽልማት ፣ ትራስፎርሜሽን ማህከል ግንባታ እና የጋራ የጥናትና ምርምር ስራዎች ላይ ያተኮረ ስምምነት መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ስምምነቱ በዘርፉ ያሉ አመራር ጉለቶችን ለመሙላት ትልቅ አስተዋፆ አለው ያሉት ሚኒስትሩ በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በሀገራችን አምራች ኢንዱስትሪውን ተወዳዳሪነትና ምራታማነት ለማሳደግ በጣም በርካታ ስራዎችን እየተሰራ ሲሆን በንቅናቄው በጥናት ከለየናችው ስራዎች መካከል አንዱ የቅንጅትና የአመራር ክፍተቶች መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡

የቅንጅት ችግሮች ከአመለካካት፣ ከአውቀትና ከቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚያያዙ ሲሆኑ ችግሮቹን ለመፍታት በአምራች ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉትን አመራሮች እና ዘርፉን የሚደግፉ ተቋማትን የአመራር ክፍተቶችን መሙላት በጣም አስፈላጊ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

እንደ ሀገር የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግር ለማምጣት የተያዘው እቅድ ውጤታማ እንዲሆን ቀጣይነት ያለው የቅንጅትና የአመራር አቅም ግንባታ ስራ ተጠናክሮ ይቀጥላል ያሉት አቶ መላኩ አለበል በተለይ አለም አቀፋዊ ሁኔታዎችን በአግባቡ ተረድቶ ምላሽ መስጠት የሚችልና ከቴክኖሎጂ ጋር በፍጥነት የሚራመድ የኢንዱስትሪ አመራር ማፍራት ለነገ የሚባል ተግባር አለመሆኑን በአፅንኦት ተናግረዋል።

የአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ፕሬዝዳንት ዛዲግ አብርሃ በበኩላቸው ዘላቂነትና ቀጣይነት ባለው መንገድ የአመራሩን አቅም ማጎልበት፣ በስልጠና የመደገፍ፣ አሰራሮችን የማሻሻል፣ እውቅና ለሚያስፈልጋቸው በመስጠት ተወዳዳሪነትን እያሳደጉ መሄድ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው ብለዋል፡፡

እንደ ሀገር የአምራች ኢንዱስትሪውን ዘርፍ ለመደግፍ ተቋማት በግል ከመስራት ይልቅ መተባርና በጋራ መስራት አስፈላጊ በመሆኑ ስምምነቱ አስፈልጓል ያሉት ፕሬዝዳንቱ ምርምርና ጥናት እንዲሁም እውቀትና ክህሎት ለሀገር እድገት እጅጉን ጠቃሚ በመሆኑ ለዚህ ብቁ የሆነ አመራርና ሠራተኛ ለመፍጠር ከተቋሙ ጋር በጋራ መስራት ያስፈልጋል ብለዋል።

ተቋማቱ በጋራ በሚሰሩባቸው ጉዳዮች ላይ ለረጅም ጊዜ ውይይት ማድረጋቸውንና ስምምነቱ በፍጥነት ወደ ትግበራ እንደሚገባም ነው ኃላፊዎቹ ያረጋገጡት።

Share this Post