የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የፈጠራቸው ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸው (የተከበሩ አቶ ዳውድ መሀመድ )

ግንቦት 15/2016 ዓ.ም (ኢሚ) ተቋሙ የተጣለበትን ኃላፊነት ለመፈፀም እየሰራቸው ባሉ ተጨባጭ የሆኑ ውጤታማ ስራዎች ለዘርፉ በፋናንስ ተቋማት ይሰጥ የነበረው የብድር ምጣኔ እንዲስተካከል፣የመንግስት ተቋማት በተናበበና በተቀናጀ መንግድ ለዘርፉ አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ቅድሚያ ሰጥተውና የጋራ እቅድ አዘጋጅተው እንዲሰሩ በማድረግ አበረታች ለውጥ እየተመዘገበ መሆኑን የኢንዱስትሪና ማዕድን ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንዱስትሪ ንዑስ ዘርፍ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ዳውድ መሀመድ ገልፀዋል፡፡

ቋሚ ኮሚቴው የተቋሙን እቅድና አፈፃፀም በቅርብ እየተከታተለ በመገምገም እየሰራ መሆኑን የገለፁት የተከበሩ አቶ ዳውድ ተቋሙ የሚሰጠውን ማስተካከያ በበጎ መንገድ በመቀበል ወደ ስራ መግባቱ የእቅድ አፈፃፀሙ የተሻለ እንዲሆን ትልቅ ሚና የነበረው መሆኑን በመጥቀስ ቋሚ ኮሚቴው ከእቅድና አፈፃፀም ሪፖርት ግምገማ ባሻገር መሬት ላይ በዘርፉ እየተሰሩ ያሉ ስራዎችን መስክ ድረስ በመውረድ ለአምራች ኢንዱስትሪዎች እየተሰጠ ያለውን ድጋፍና ክትትል በመመልከት ጠንካራ ጎኖች እንዲቀጥሉ ያጋጠሙ ችግሮች በውል ተለይተው መፍትሔ እንዲሰጣቸው ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ጋር በቅርበት እየሰራ በመሆኑ የአምራችቾ የማምረት አቅም አጠቃቀም እየተሻሳለ መምጣቱን ማረጋገጥ መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የገቢና ወጭ የምርት ምጣኔን በማስተካከል ሀገራዊ የንግድና የኢኮኖሚ ሚዛኑን ለማስተካከል የሚደረገውን ጥረት ከግብ በማድረስ ሀገራዊ ብልፅግናችንን እውን ለማድረግ የኢትዮጵያ ታምርት ሀገራዊ ንቅናቄ የፈጠራቸው ቅንጅታዊ አሰራሮች ተጠናክረው መቀጠል አለባቸውም ብለዋል፡፡

አክለውም የሀገራችን የምርት ጥራት እንዳለው ተከታታይ የሆነ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ በመስራት ዜጎች ለሀገራቸው ምርት ያላቸውን ግንዛቤ በማሻሻል በራሳቸው ምርት እንዲጠቀሙ ለማድረግ መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post