በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ የምርምር የልዕቀት ማዕከላት ላይ ውይይት ተካሄደ።

ግንቦት 15/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ) ውይይቱ ከዚህ ቀደም የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ፣ የቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ (CIDCA) እና የተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (UNIDO) በጋራ ለመስራት የፈረሙትን የሶስትዮሽ ስምምነት መሠረት ያደረገ ነው፡

በአምራች ኢንዱስትሪ ላይ ያተኮረ የምርምር የልዕቀት ማዕከላቱ የሚቋቋሙበት ቦታ፣ የፕሮጀክት ስያሜን በተመለከተ እና ፕሮግራሙ ይፋ የሚሆንበት ቀን የውይይቱ ዋና አጀንዳዎች ሲሆኑ በውይይቱ የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ፣በቻይና ዓለም አቀፍ ልማት ትብብር ኤጀንሲ ምክትል ዋና ዳይሬክተር የተመራ ቡድን እና ከተባበሩት መንግስታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት ምክትል ዋና ዳይሬክተር እና ዳይሬክተር ተሳታፊ ሆነዋል፡

Share this Post