የህዝብ ግንኙነትና ኮምዩኒኬሽን ስራ ለኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ መሳካት ወሳኝነት ነዉ (አቶ ሀሰን መሃመድ )
የኢፌዴሪ ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በስሩ ለሚገኙ ከፍተኛና መካከኛ አመራሮች በኮምዩኒኬሽን ፅንሰ ሃሳብና ስትራቴጂያዊ ኮምዩኒኬሽን በተለይም በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ላይ የሚያመጣውን ተፅኖ በተመለከተ ስልጠና እየተሰጠ ነዉ።
የስልጠናዉ ዋና አላማም ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሩ በኮምዩኒኬሽን ፅንሰ ሃሳብ ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሮት ተቋሙንና የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን የተመለከቱ መረጃዎችን በአግባቡ ተደራሽ ለማድረግ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሀሰን መሀመድ ገልፀዋል።
የኮምዩኒኬሸን ዘርፉ የሚመራበት ስትራቴጂ ካለመኖሩ ጋር ተያይዞ በርካታ ችግሮች እንደሚስተዋሉ የገለፁት አቶ ሃሰን ችግሮቹን ለመቅረፍ አንደተቋም የኮምዩኒኬሽን ስትራቴጂ ተዘጋጅቶ ወደ ስራ መገባቱን እና ይህም ካሉት የፌደራል ተቋማት መካከል ቀዳሚውን ስፍራ እንዲይዝ አድርጎታል ሲሉ አክለዋል።
የአምራች ኢንዱስትሪ መረጃዎችን ተደራሽ ለማድረግም ደረጃውን የጠበቀ ስቱዲዮ ተገንብቶ ወደ ስራ ለመግባት ዝግጅት መጠናቀቁን የጠቆሙት ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን ከግምት ውስጥ በማስገባት በየደረጃው የሚገኙ ኃላፊዎች ዘርፉን የሚመለከቱ መረጃዎች ለመገናኛ ብዙሀን በመስጠጥ መረጃን ተደራሽ በማድረግ የበኩላቸውን ሚና እንዲወጡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት