የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሀመድ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የምግብ ድርጅት የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ የአገልግሎት አስተዳደር ጆቫኒ ሙንዞ የተመራ ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል።
ግንቦት 27/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ)የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሃሰን ሙሀመድ በተባበሩት መንግስታት አለም አቀፍ የምግብ ድርጅት የምስራቅ እና ደቡብ አፍሪካ የአገልግሎት አስተዳደር ጆቫኒ ሙንዞ የተመራ ቡድን ተቀብለው አነጋግረዋል። አለም አቀፍ የምግብ ድርጅት ኢትዮጵያ በሥነ-ምግብ ራስዋን እንድታሻሸል ፣የግብርና ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ ፣የነዋሪዎችን የኑሮ ደረጃ ከፍ ለማድረግ ከሚያደርገው ድጋፍ ጎን ለጎን ጥራት ያላቸውንና ተወዳዳሪ የሆኑ የግብርና ምርቶች ለአለም አቀፍ ገበያ እንድታቀርብ፣ የተቀናጁ የግብርና ምርቶች ማቀነባበሪያ ፓርኮች የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።
በዉይይቱም ሉዑካኑ ዘርፉን ለመደገፍ ዝግጁ መሆናቸዉን ገልጸዎል።