የህዝብ ግንኙነትና ተግባቦት ስራ ከተቋም በዘለለ በየእለት ተእለት የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ላይ ተዕእኖ ፈጣሪ ነው (ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ)

የህዝብ ግንኙነትና ተግባቦት ስራ ከተቋም በዘለለ በየእለት ተእለት የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ላይ ተዕእኖ ፈጣሪ ነው (ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ)

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ የተሳለጠ የመረጃ ስርአት አና ተደራሸነትን ለማጠናከር በየደረጃው ላሉ አመራሮች በህዝብ ግንኙነትና ተግባቦት ጽንሰ ሃሳብ ላይ ስልጠና ሰጥቷል።

በኮምዩኒኬሽን እና ስትራቴጂክ ኮምዩኒኬሽን ፅንሰ ሃሳቦች ላይ ስልጠና የሰጡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ረ/ፕሮፌሰር ዶ/ር ጌታቸው ድንቁ የህዝብ ግንኙነትና ተግባቦት ስራ ከተቋም በዘለለ በየእለት ተእለት የሰው ልጅ እንቅስቃሴ ላይ ተዕእኖ ፈጣሪ በመሆኑ ሁሉም እንደየተመደበበት የስራ ኃላፊነት የመረጃ ባለቤት መሆኑን አምኖ ዘርፉን የተመለከቱ መረጃዎችን በአግባቡ ተደራሽ የማድረግ ሃላፊነት እንዳለበት ገልፀዋል።

በስልጠናው የኮምዩኒኬሽን እና ተግባቦት ምንነት፣ አስፈላጊነት፣ የኢንዱስትሪ ዘርፍ የኮምዩኒኬሽን ስትራቴጂ መመሪያ ላይም ማብራሪያ ተሰጥቷል።

Share this Post