በአምራች ኢንዱሰትሪ ለተመዘገበው የተሻለ አፈፃጸም የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ሚና አስተዋፆ... አበርክቷል (አቶ መላኩ አለበል)

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከአጠቃላይ ሰራተኞቹ ጋር በ2016 በጀት የ10 ወራት አፈጻጻምና በ2017 በጀት እቅድ ዝግጅት ላይ ውይይት እያካሄደ ነው።

እየተገባደደ ባለው 2016 በጀት አመት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ጥሩ የሚባል አፈፃጸም ማምጣቱን የገለጹት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ለዚህም በዝግጅት ምዕራፍ ከፌደራል ጀምሮ እስከ ክልልና ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪ ቢሮዎች የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች፣እንደ ሀገር ለተጀመረው የኢትዮጵያ ታምርት ኤክስፖ ባለድርሻ አካላት በቂ ድጋፍ ማድረጋቸው፣እንደ ሀገር ከፖሊሲ ዝግጅት ጀምሮ ለዘርፉ መነቃቃት የተደረጉ ማሻሻያዎች እንዲሁም የተቋሙ አጠቃላይ ሰራኞች አቅም በመገንባቱ ለዘርፉ አፈፃጸም መሻሻል ምክንያት መሆኑን ጠቁመዋል።

በ2016 በጀት በዘርፉ የታየው አፈፃጻም መልካም ቢሆንም የሚቀሩ ስራዎች እንዳሉ የገለፁት አቶ መላኩ በ2017 በዘርፉ የማምረት አቅም አጠቃቀምን በማሳደግ፣ተኪ ምርቶችን በማሰደግ፣ለዜጎች የስራ እድል በመፍጠር የምርምር ማእከላትን በማጠናከርና ለዘርፉ የሚሰጡትን ፋይዳ በማጎልበት እና ወጪ ምርትን በማሰደግ ረገድ ትልቅ ስራ የሚጠበቅ በመሆኑ ሁሉም ፈፃሚ የድርሻውን በመወጣት ዘርፉ በሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ላይ ያለውን አስተዋፅኦ ማሳደግ እንደሚጠበቅበት አክለዋል።

በውይይቱ የዘርፉ 2016 በጀት የ10 ወራት አፈፃጸምና የ2017 በጀት እቅድ ቀርቦ ውይይት ይካሄድበታል።

Share this Post