በእውቀት ላይ የተመሰረተ ክትትልና ግምገማ ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ እድገት ወሳኝነት አለው።

ሰኔ 08/2016 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ለሚኒስቴር መስሪያ ቤቱና ተጠሪ ተቋማቱ አመራሮች የአምራች ኢንዱስትሪዎች የክትትልና ግምገማ መመሪያ ዙሪያ ስልጠና እየተሰጠ ነው።

የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ ለሀገራችን ኢኮኖሚ ዕድገት የሚያበረክተውን አስተዋፅኦ ከፍ በማድረግ በዕውቀት ላይ የተመሰረተ ወጥነት ያለው ክትትልና ግምገማ ለዘርፉ ዕቅድ ስኬት ሚናው የላቀ በመሆኑ የአሰራር መመሪያ የተዘጋጀ መሆኑን የገለፁት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሀዱሽ ሀለፎም መመሪያውን ሁሉም የሚመለከተው አካል እንዲያውቀው ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ይሰራል ብለዋል።

የክትትልና ግምገማ ፅንሰ ሀሳብ አተገባበርና ፋይዳው ዙሪያ ስልጠና የሰጡት የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ እሸቱ ስጦታው በበኩላቸው የአንድ ተቋም የዕቅድ ስኬትና ውድቀት የሚወሰነው በሚተገብረው የክትትልና ግምገማ ስርዓት መሆኑን ገልፀዋል።

ዋና ስራ አስፈፃሚው አክለውም የክትትልና ግምገማ ስርዓት በስራ ወቅት ለሚገጥሙን ችግሮች የመፍቻ ቁልፍ ነው።

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post