አምራች ኢንዱስትሪዎች በስራ ላይ እያጋጠማቸዉ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ የመስክ ጉብኝት ተካሄደ።

ሰኔ 7/2016ዓ.ም የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እና የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ቴክኖስተይል የፈርኒቸር ማምረቻን ጎብኝተዋል። በተመሳሳይ የሸገር ከተማ ምክትል ከንቲባ እና የከተማዉ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ዜድኤም ትሬዲንግ ተጎብኝቷል።

የመስክ ጉብኝቱ ዋና ዓላማ የአምራች ኢንዱስትሪዎች በስራ ላይ እያጋጠማቸዉ ያሉ ተግዳሮቶችን በቅርበት ለይቶ ለመፍታት እና ዘርፉን ለማበረታታት ያለመ ነው፡፡ ጉብኝቱ አምራች ኢንዱስትሪዎችን የስራ እንቅስቃሴ በማየት የማምረት አቅምና የምርት ጥራትን ሊያሳድግ በሚያስችል መንገድ ለመደገፍ መሆኑ የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ተናግረዋል።

ኢንዱስትሪዎቹ የሀገር ዉስጥ ምርት መተካት፣ተጨማሪ የስራ እድል ፈጠራ እና የዉጪ ምንዛሬ ማዳን ላይ ከፍተኛ ሚና እንዳላቸዉም ገልጸዎል።ኢንዱስትሪዎቹ ያሉበት ደረጃ አበረታች እንደሆነ የገለጹት ሚኒስትሩ የውጭ ምንዛሬ ገቢ በማስገባት ትልቅ አስተዋጽኦ ያላቸዉ በመሆኑ መንግስት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል እና በቅንጅታዊ አሰራር መፍታት የሚገባቸው ችግሮች ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሌሎች ተቋማት ጋር በጋራ ለመፍታት እንደሚሰራ ገልጸዋል፡፡

Share this Post