የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በመልካም አስተዳደር አፈፃፀም ምዘና ከፍተኛ አፈፃፀም ላስመዘገበው ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ዕውቅና ሰጠ

ሰኔ 11/2016ዓ.ም (ኢ.ሚ)የመንግሥት መሥሪያ ቤቶችን የመልካም አስተዳደር አፈፃፀም በመለካት በሚያስመዘግቡት ዉጤት መሠረት ማበረታቻ በመስጠቱ የአገልግሎት አሰጣጥ ስርዓታቸውን ይበልጥ እንዲያሻሽሉ ለማድረግ ተነሳሽነትን መፍጠር መሆኑን የኢትዮጵያ ህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ዘውዱ ወንድሙ ገልፀዋል፡፡

ተቋሙ አምስቱ የመልካም አስተዳደር በተመረጡት መለኪያዎች በስራቸው 26 አንኳር ጥያቄዎች እና 86 ንዑሳን ጥያቄዎችን በማዘጋጀት በ2015/16 ለተከታታይ 10 ወራት በ15 ሚንስቴር መ/ቤቶች በጋይድ ላይኑ መሰረት የምዘና ልኬት እና ደረጃ ማውጣት ስራዎች መሰራቱን ተናግረዋል ።

በምዘናውም የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሶስተኛ ደረጃ በመውጣት የዋንጫና ሰርተፍኬት ተሸላሚ መሆኑን የገለፁት አቶ ዘውዱ የመልካም አስተዳደርን ለማስፈን ወጥነት ያለው የተጠያቂነት ሥርዓትን በመዘርጋት ከተመዘኑት የፌደራል ተቋማት መካከል ተቋሙ የተሻለ አፈፃፀም እንደነበረው ጠቁመዋል፡፡

መልካም አስተዳደር በሕዝብና በመንግስት መካከል ጠንካራ መተማመን እንዲኖር ያደርጋል ያሉት አቶ ዘውዱ ምዘናው ለመልካም አስተዳደር መሻሻል ትልቅ አስተዋፅኦ እንደሚኖረው ተናግረዋል።

በምዘናው ደረጃ ያገኙ ሁሉም ተቋማት ከሌሎች ተሽለው የተገኙ እንጂ፣ የመልካም አስተዳደር ችግር የሌለባቸው ናቸው ማለት እንዳልሆነ ግንዛቤ ሊወሰድ እንደሚገባም አሳስበው የተጀመሩ አበረታች የመልካም አስተዳደር ስራዎች አጠናክሮ በማስቀጠል አርዓያነት ያለው ተቋም ሆኖ መቀጠል ያስፈልጋል ብለዋል።

Share this Post