በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነነት ለመፍታት የሚደረጉ ጥረቶች ተጠናክረው ይቀጥላሉ (አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ)
ነሐሴ 20/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከክልልና፣ ከተማ አስተዳደር፣ ተጠሪ ተቋማትና ባለድርሻ አካላት ጋር የ2016 በጀት ዓመት እቅድ አፈጻጻምና የ2017 ዕቅድን ገምግሟል።
በመድረኩ የተሳተፉ የዘርፉ አመራሮች እንደተናገሩት በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በርካታ ስኬቶችን ማስመዝገብ እንደቻሉ ገልጸዋል።
ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር በኢንዱስትሪው ዘርፍ የሚስተዋሉ ችግሮችን በዘላቂነት ለመፍታት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀትና የሚያደርጋቸውን ድጋፍና ክትትል በተጠናከረ መልኩ እንደሚቀጥል የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ታረቀኝ ቡሉልታ ጠቁመዋል።
በጀት ዓመቱ እንደ ሀገር የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን አቅጣጫ በመቀበል በክልልና በከተማ አስተዳዳር በማከናወን ዘርፋን የማነቃቃት፣ የሚስተዋሉ ችግሮችን በመፋታት፣ የሀገር ውስጥ አምራቾች ምርቶቻቸውን እንዲያስተዋውቁ ከፋተኛ ሚና ነበረው ብለዋል።
ተሳታፊዎቹ በበኩላቸዉ የሚስተዋሉ የመሰረተ ልማት በተለይም የኤሌትሪክ፣ የብድር አቅርቦት፣ የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሸን አገልግሎት የሚሰጡ ባለሙያዎች የክህሎት ክፍተቶችን እንደ ችግር አንስተዋል።
የአምራች ዘርፉ ይበልጥ ውጤታማ ለማድረግ ከቴክኒክና ሙያ እና ከከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ገልፀዋል።