ለሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ዘርፉ የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ሊያሳካ የሚችል ፖሊሲና የፖሊሲው ማስፈፀሚያ ስትራቴጅዎች ተቀርፀው ወደ ስራ መገባቱን ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጹ
ነሐሴ 21/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢትዮጵያ ታምርት ሀራዊ ንቅናቄ ዘርፉ በየደረጃው ያሉ የፖለቲካ አመራሮች ቁርጠኝነት እንዲኖር፣ የመሰረተ ልማት ፣ የፋይናንስ እና የምርምርና ጥናት ተቋማትን ድጋፍና ትኩረት እንዲያገኝ በማስቻል ትልቅ አስተዋፅኦ ማበርከቱን የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ገልፀዋል፡፡
ንቅናቄው ሀገራዊ መግባባት የተያዘበት አጀንዳ ነው ብሎ መውሰድ ይቻላል ያሉት ሚኒስትሩ ሰዎች በፖለቲካ ፣በሀይማኖት፣ በአካባቢ፣ በፆታ ወይም በሌላ ልዩነታቸውን ያላሳዩበት አጀንዳ መሆኑን ገልጸው የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ አስፈላጊነትና የወደፊት የኢትዮጵያ ዕጣ ፈንታ የሚወስን መሆኑ ላይ ግልፅ የሆነ መግባባት ላይ መደረሱንም ጠቁመዋል፡፡
ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገት ዘርፉ የሚጠበቅበትን አስተዋፅኦ ሊያሳካ የሚችል ፖሊሲና የፖሊሲው ማስፈፀሚያ ስትራቴጅዎች ተቀርፀው ወደ ስራ የተገባ በመሆኑ ዘርፉ ተስፋ ሰጭ እድገት እያስመዘገበ መሆኑን ገልጸው ለሀገራዊ ዓላማ የሚተጋ አመራርና ባለሙያ በመገንባት ዘርፉን የተሻለ ኢኮኖሚያዊ ፋይዳ እንዲኖረው ለማድረግ እየተሰራ ነው ሲሉም አንስተዋል፡
ሚኒስትሩ አክለውም 2016 በጀት ዓመት በተለያዩ ሀገራዊና ዓለማቀፋዊ ተፅዕኖዎች ምክንያት ስራ አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ የገቡበት፣ ገቢ ምርትን በሀገር ውስጥ ማምረት የተቻለበት፣ከየፌዴራል እስከ ክልልና ከተማ አስተዳደር ያሉ አመራሮች ለዘርፉ ትኩረት የሰጡበት፣ የዘርፉ ማስፈፀሚያ ፖሊሲ፣ ስትራቴጅዎች፣ መመሪያዎች ተዘጋጅተው ወደ ስራ የገቡበት ፣ለበርካታ ዜጎች የስራ እድል የተፈጠረበት ነው ሲሉም ገልጸዋል፡፡
በመጨረሻም በቅንጅት ተናቦ እና ተግባብቶ በጋራ አቅዶ መስራት ከተቻለ ምንም አይነት ፈተና ቢገጥመን በምንም አይነት ፈታኝ ዓለማቀፋዊ እና ሀገራዊ ችግሮች ውስጥ ብንሆንም ከችግሩ በላይ ሆነን ያቀድነውን እንደምናሳካ ያረጋገጥንበት በጀት ዓመት ነው ብለዋል፡፡
All reactions:
3232