የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን በጋራ ለመስራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሄዱ

የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል በኢትዮጵያ የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ፀኃፊ ክሌቨር ጋትት እና የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ቀጠናዊ ትስስርና የንግድ ልውውጥ ዳይሬክተር ስቴፈን ካረንጊን በፅ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል ።

በውይይታቸው የኢትዮጵያ መንግስት ለአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፉ የሰጠውን ትኩረት፣ አምራች ኢንዱስትሪው ለሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገት ፣ለስራ እድል ፈጠራና አለማቀፋዊ ተወዳዳሪነትን ከማሳደግ አንፃር የሚጫዎተውን ሚና ዘርፉን ለማሳደግ በሚደረጉ ጥረቶች እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችን በተመለከተ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ማብራሪያ ሰጥተው ኮሚሽኑ አምራች ኢንዱስትሪውን ለማሳደግ በሚደረገው ጥረት የቴክኒካል፣ፋይናንስ፣ የዘርፉን የምርታማነትና የፈጠራ ስራ የሚያግዙ የአቅም ግንባታ ስራዎችና ሌሎች የአምራች ዘርፉን በሚያሳድጉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡

የተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን የኢትዮጵያ አምራች ኢንዱስትሪ በተለይም የቆዳ ዘርፉን ምርጥ ተሞክሮዎች በመቀመር የተሻለ ስራ ለመስራት ከኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ጋር የቴክኒክና የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ በጋራ በትብብር ለመስራት ተስማምተዋል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት #እኛም_እንሸምት

Share this Post