የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ከማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ከፍተኛ የመንግስት ሃላፊዎች ፣የዞን እና ልዩ ወረዳ አስተባባሪዎች ጋር በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ፡፡

መስከረም 24/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች ከማዕከላው ኢትዮጵያ ካቢኔ ፣የዞኑ እና ልዩ ወረዳ አስተዳዳሪዎች ጋር በኢንዱስትሪ ዘርፍ ላይ ያተኮረ ውይይት አካሄዱ፡፡

ውይይቱ በክልሉ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ያለበትን ሁኔታ ፣ ለአምራች ዘርፉ ያሉ ምቹ ሁኔታዎች እና የቀጣይ ስራዎች ላይ ዓላማ ያደረገ መሆኑን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ገልጸዋል፡፡

በሰባት ዞን ከ1,600 በላይ መሬት በማዘጋጀት በክልሉ ያሉ የማኒፋክቸሪንግ ዕድሎችን ባለሀብቶች እንዲጠቀሙ እና ክልሉን የማኒፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ማዕከል የማድረግ ህልም ይዘው እየሰሩ ያሉት ስራ ለሌሎች ክልሎች ተሞክሮ የሚሆን ነው ብለዋል፡፡

የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ እንደሻው ጣሰው በበኩላቸው ህልማችንን እውን ለማድረግ በክልሉ የሚገኙ ጸጋዎችን በመጠቀም ክልሉን የማኒፋክቸሪንግ የኢንዱስትሪ ማዕከል ለማድረግ እየሰራን ነው ፣ለዚህም በየደረጃው ያለው አመራር ለኢንዱስትሪው ትኩረት ሰቶ የበኩሉን ሚና መወጣት አለበትም ሲሉ ገልጸዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒሰቴር እና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮች በማዕከላው ኢትዮጵያ በቡታጅራ የሚገኘውና ለ1ሺ ዜጎች ስራ እድል የፈጠረው፣ ለአሜሪካ እና አውሮፓ ምርቶችን የሚያቀርበው ሀገር በቀሉን ደስታ ጋርመንት እና ወራቤ የሚገኘውን የኢንዱስትሪ መንደር ጎብኝተዋል፡፡

#WorldWithoutHunger #SustainableDevelopment #EndHunger #SDGs #aworldwithouthungerispossible

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post