የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማን ናቸው?

የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ የተወለዱት በደባርቅ ሰሜን ጎንደር ነው፡፡

የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በፖለቲካ ሳይንስ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት አግኝተዋል።

እንግሊዝ ከሚገኘው ላንክስተር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በዓለም አቀፍ ግንኙነት እና በስትራቴጂ ጥናት ሁለተኛ ድግሪያቸውን ወስደዋል።

በተለያዩ ሀገራት አጫጭር የዓለም አቀፍ ግንኙነት እና ፖለቲካል ሳይንስ ሥልጠናዎችን እና ኮርሶችን ወስደዋል።

አምባሳደር ታዬ፤ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአውሮፓ መምሪያ የሥራ ክፍል ፣የምዕራብ አውሮፓ ዋና ክፍል ኃላፊ፣የኢንፎርሜሽን ተጠባባቂ ዳይሬክተር፣ስቶክሆልም የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት፣በዋሽንግተን የኢፌዲሪ ኤምባሲ በአማካሪነት።

በሎስአንጀለስ ቆንስል ጀነራል፣ በ1998ዓ.ም ባለሙሉሥልጣን አምባሳደርነት ተሹመዋል፣

በሎስአንጀለስ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት ማዕረግ የቆንስላ ጽ/ቤት ኃላፊ፣ በአውሮፓ እና አሜሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጀኔራል፣ በ2008 ዓ.ም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው ሰርተዋል።

በግብፅ የኢትዮጵያ ባለሙሉ ሥልጣን አምባሳደርነት፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ተጠሪ ሆነው አገልግለዋል።

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ሰርተዋል፤

አምባሳደር ታዬ እስከዛሬዋ ዕለት ድረስም የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ሠርተዋል።

Share this Post