የአዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ማድረግ ያስፈልጋል።
ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የትራንስፖርት ሴክተሩን ችግር ለመፍታት እንዲያስችል አገልግሎት ሰጥተው ያቆሙ አውቶብሶችን መልሶ በመጠቀም በተሻለ አቅም ማገልግል እንዲችሉ የሚያስችል የውይይት መድረክ ላይ የኢንዱስትሪ ሚኒስቴርን በመወከል የአምራች ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚልኬሳ ጃገማ የአዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ዘርፍ ምቹ ሁኔታ በመፍጠር ለሀገር ኢኮኖሚያዊ ሽግግር ከፍተኛ ሚና እንዲጫወት ማድረግ ያስፈልጋል ብለዋል።
መንግስት የአምራች ኢንዱስትሪ ዘርፍ ለማሳደግ የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄን በማዘጋጀት የሀገር ውስጥ ኢንዱስትሪዎችን የማምረት አቅም ለማሳደግ፣ ከውጭ የሚገቡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ ምርት ለመተካት ፣ለዜጎች የስራ ዕድል ለመፍጠር ፣ የሀገር ውስጥ አምራቾችን የእርስ በርስ ትስስር ለማጠናከር ትኩረት በማድረግ እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል ።
በተለይም በተኪ ምርት ላይ ለተሰማሩ አምራች ኢንዱስትሪዎች ትልቅ ድጋፍ እያደረገ መሆኑን የጠቀሱት ዳይሬክተሩ የአዉቶሞቲቭ ዘርፋን ለማጠናከር የቴክኖሎጂ ሽግግር በማድረግ ፣ የስራ ዕድል በመፍጠር የኢትዮጵያ ታምርትን በተግባር እያሳየ የመጣበት ሁኔታዎች ተጠናክረው ሊቀጥሉ እንደሚገባም ተናግረዋል።
ፍራንኩን ኢት አዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር ዘርፋን ለማሳደግ እየሰራው ያለው ተግባር በዘርፋ ላሉ ሌሎች አምራቾች አርያ መሆኑን ያነሱት ዶ/ር ሚልኬሳ ጃገማ ሁሉም ባለድርሻ አካላት የትራንስፖርት ሴክተሩን ችግር ለመፍታት እንዲያስችል የበኩልን አስተዋጽኦ እንዲያበረክት አሳስበዋል ።
አገልግሎት ሰጥተው ያቆሙ አውቶብሶችን መልሶ በመጠቀም በተሻለ አቅም ማገልግል እንዲችሉ ማሳያ ይሆን ዘንድ በፍራንኩን ኢት አዉቶሞቲቭ ኢንጂነሪንግ እና የትራንስፖርት ፌዴሬሽን በቅንጅት የጀመሩትን ሀገራዊ ስራ የተገኘው ውጤት አበረታች በመሆኑ በማጠናከር ተሞክሮውን የማስፋቱ ተግባር ተጠናክሮ ሊቀጥል ይገባል ብለዋል።
#ኢትዮጵያ_ታምርት
#እኛም_እንሸምት