የማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂዎች (ማኑ ቴክ) ማዕከል ከ10 አስተናጋጅ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አትዮጵያ አንዷ ሆና ተመርጣለች
ነሐሴ 29/2016ዓ.ም(ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል አትዮጵያ በማኑፋክቸሪንግ ቴክኖሎጂዎች (ማኑ ቴክ) ማዕከል ከ10 አስተናጋጅ የአፍሪካ ሀገራት መካከል አንዷ ሆና በመመረጧ የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ሳሙኤል ግባይዲ ዶኢ በፅ/ቤታቸው በመቀበል በቀጣይ ስራዎች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይታቸው የኢትዮጵያ መንግስት እንደ አስተናጋጅ በዘርፍ ያላትን የንፅፅር ጥቅም በመጠቀም በቴክኖሎጂ የተደገፉ መፍትሄዎችን በማዘጋጀት የሀገር ውስጥ እና አህጉራዊ የማኑፋክቸሪንግ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እንደምትሰራ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል ማብራሪያ ሰጥተዎል።
እንደ ስልጠና መስጫና የውድድር ማዕከል አድርጋ የምትጠቀመው በሚኒስቴር መስራያቤቱ ያሉትን የአምራች ኢንዱስትሪ ማዕከላትን መሆኑንም አስረድተዋል፡፡
ማዕከላቱ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ እና የአስር አመት የልማት እቅድን ጨምሮ፣ በኢንዱስትሪ እድገት፣ በስራ እድል ፈጠራ እና ምርታማነትን ማሳደግ ላይ ያተኮረ ከኢትዮጵያ አስከ ሀገራዊ ግቦች ጋር ለማጣጣም የሚረዱ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡
በማኑፋክቸሪንግ ሴክተር ውስጥ ወጣቶችና ጀመሪ የስራ ፈጠሪዎች በመላው አፍሪካ ከፍተኛ ተጽዕኖ ፈጣሪ በመሆን መስፋፋት እንዲችሉ ለማድረግ መሆኑን ገልፀዋል።
ማዕከላትን ለማጠናከር የ1.5 ሚሊዮን ዶላር የመጀመሪያ ኢንቨስትመንት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የተፈፀመ ሲሆን ተጨማሪ የገንዘብ ድጋፍ ከመንግስት እና ከግል አጋሮች እንደሚፈለግ አስረድተዋል።
የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ በመላው አፍሪካ የስራ ፈጠራን ለማጎልበት የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም ቲምቡክቱ ተነሳሽነት ጋር በማጣጣም ተግባራዊ ለማድረግ ይሰራ ብለዋል።
የተባበሩት መንግስታት የልማት ፕሮግራም የኢትዮጵያ ተወካይ አቶ ሳሙኤል ግባይዲ ዶኢ በበኩላቸው አዳዲስ ስራ ፈጣሪ ወጣቶችን ከተለያዩ የአፍሪካ ሀጋራት በማሳተፍ የእራሳቸውን እውቀት የሚያሳድጉበትና ልምድ በማለዋወጥ የተሻለ ውጤት ያመጡትን የ25,000 የአሜሪካ ዶላር ተሸላሚ ይደረጋል ብለዋል፡፡
አፍሪካ የማምረቻ ቴክኖሎጂዎች ቀዳሚ እንድትሆን በማድረግ አህጉራዊና ዓለም አቀፍ ኢንቨስትመንቶችን ለመሳብ ከፍተኛ አስተዋፅዖ እንደሚኖረው ጠቁመው ከቀጣዩ የፈረንጆች አዲስ ዓመት በኋላ ተግባሪዊ እንደሚደረግ አስረድተዋል፡፡
All reactions:
4040