አምራች ኢንዱስትሪው 10.4% አማካይ ዕድገት አስመዝግቧል (አቶ ጥላሁን አባይ)

ሀምሌ 17/2017 ዓ.ም (ኢ.ሚ) በ2017 በጀት ዓመት በተሰሩ ውጤታማ ተግባራት የአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ 10.4% አማካይ ዕድገት እንዳስመዘገበ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ጥላሁን ዓባይ ተናገሩ፡፡

ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ለውይይት መነሻ የሚሆን የአፈፃጸም ሪፖርት ያቀረቡት አቶ ጥላሁን አምራች ኢንዱስትሪው ለሀገራዊ ኢኮኖሚ ጉልህ ፋይዳ ስላለው በ2018 ዓ.ም 162 አዳዲስ አምራች ኢንዱስትሪዎችን ወደ ስራ ለማስገባትና የዘርፉንም ዕድገት 10.7% ለማድረስ እንደታቀደ ገልጸዋል፡፡

ስራ አስፈፃሚው በ2017 በጀት ዓመት በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ ለ352,513 (ሶስት መቶ አምሳ ሁለት ሺህ አምስት መቶ አስራ ሶስት) ዜጎች የስራ ዕድል እንደተፈጠረ ገልፀው በ2018 በጀት ዓመት ከኤክስፖርት 570 ሚሊዮን ዶላር ለማግኘት መታቀዱንና በፊት ከነበሩት በተጨማሪ 15 አዳዲስ ምርቶችን ወደ ኤክስፖርት ለማስገባት መታቀዱን ጠቁመዋል ፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post