የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓልን በተለያዩ ፕሮግራሞች አከበረ

የካቲት 21/6/2017ዓ.ም (ኢ.ሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከተጠሪ ተቋማቱ ጋር በመሆን 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓልን "ዓድዋ የጥቁር ህዝቦች ድል" በሚል መሪ ቃል አከበረ፡፡

የቀደሙ አባቶች ለሀገርና ለትውልድ ግንባታ ትልቅ ትርጉም ያለውና ዘመን የማይሽረው ታሪክ በመስራት ባህላችን፣ ቋንቋችን፣ ራሳችን የማስተዳደር ስልጣን እና ታሪክ ያለን ጥንታዊና ድል አድራጊ ሃገር ሆነን እንድንታይ አድረገዋል፡፡

በአንድነት ፣በጋራ እና በሀገር ፍቅር ስሜት በጋራ በመስራት እንደ ሀገር የተያዙ ዕቅዶችን በመተግበር እንደተቋም የተቀመጡ ተግባርና ሀላፊነትን በመወጣት ለሀገር እድገት መስራት ያስፈልጋል በሚል 129ኛዉ የዓድዋ ድል በዓል የተከበረ ሲሆን በእለቱም የጥያቄ እና መልስ ውድድር በማድረግ ተከብራል፡፡

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post