ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር 1446ኛውን የኢድ አልፈጥር በአልን አስመልክቶ ማዕድ አጋራ

መጋቢት 20/2017 ዓ.ም (ኢሚ) የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ሪፎርም ፕርፎርማንስ ፕሮጀክት 1446ኛውን የኢድ አልፈጥር በዓልን አስመልክቶ በሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ለሚገኙ አባዎራዎች ማዕድ አጋራ ።

ፕሮጀክቱ በሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ሲቲ ዞን ሽንሌ ወረዳ ለሚገኙ ሶስት መቶ አባዎራች በገንዘብ 1 ሚሊየን ብር የሚገመት የፓስታ ፣የስንዴ ዱቄት እና የምግብ ዘይት ድጋፍ አድርጓል።

የአየር ንብረት ለውጥ ሴክተር ፕርፎርማንስ ፕሮጀክት በተለይም በአፋርና ሶማሌ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት በዋናነት ከሚሰራዎች ስራዎች ጎን ለጎን የተለያዩ ሰው ተኮር ተግባራትን በማከናወን ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ አንደሚገኝ የፕሮጀክቱ ማናጀር አቶ ዳዊት አለሙ ገልጸዋል።

ቅዱስ በሆነው የረመዳን ወር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ያደረገው ድጋፍ ወሳኝ መሆኑን የክልሉ ሲቲ ዞን ም/አስተዳዳሪ አቶ ሙሃመድ አብዱራህማን ገልፀዋል።

የሶማሌ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ኢንዱስትሪና ኢንሸስትመት ቢሮ ኃላፊ አቶ ኢብራሂም መሃመድ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ በክልሉ ሲቲ ዞን ጂረኒ ቀበሌ ለሚገኙ ዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላላቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ያደረገው ድጋፍ በአስፈላጊው ጊዜና ሰዓት የተሰጠ ነው ሲሉ በመግለፅ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

#ኢትዮጵያ_ታምርት

#እኛም_እንሸምት

Share this Post