በኮምቦልቻ ከተማ 145 ኢንዱስትሪዎች የሚሳተፉበት የኢትዮጵያ ታምርት ክልላዊ የማጠቃለያ መድረክ ዛሬ ይካሄዳል።

ባሕር ዳር፡ ግንቦት 30/2018 ዓ.ም (አሚኮ) በዚህ መድረክ ላይ ለመታደም ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል እና ሌሎችም ከፍተኛ መሪዎች ተገኝተዋል። ክልላዊ የንቅናቄ ማጠቃለያ መርሐ ግብሩ "ኢትዮጵያ ታምርት ለሁለንተናዊ ሉዓላዊነት" በሚል መሪ መልዕክት ነው የሚካሄደው።

በክልሉ ውስጥ የሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸውን አቅርበው የሚያስተዋውቁበት እና የሚሸጡበት ኤክስፖም ተዘጋጅቷል።

ንቅናቄው አምራቾች ምርታቸውን እንዲያስተዋውቁ፤ የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እና ችግሮቻቸውን ተቀርፈውላቸው የተሻለ እንዲያመርቱ የሚያስችል ነው።

በኤክስፖው 145 ኢንዱስትሪዎች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

አሚኮ እንደገለጸዉ ርዕሰ መሥተዳድሩ በቆይታቸው "ኢትዮጵያ ታምርት" ክልላዊ የማጠቃለያ መርሐ ግብር ኤክስፖን ይከፍታሉ፤ ከባለሀብቶች እና ከባለድርሻ አካላት ጋርም ይወያያሉ።

Share this Post