ባለፉት አስር ወራት 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት ተችሏል - አቶ መላኩ አለበል

ሠኔ 07/2016 ዓ.ም (ኢ.ሚ)በበጀት ዓመቱ ባለፉት አስር ወራት 2 ነጥብ 2 ቢሊዮን ዶላር የሚያወጡ ምርቶችን በሀገር ውስጥ መተካት መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል ተናገሩ።

.

የ2016 በጀት ዓመት የመጨረሻ የ100 ቀናት አፈጻጸም ግምገማ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል።

የኢንዱስትሪ ሚኒስትሩ አቶ መላኩ አለበል የኢንዱስትሪ ዘርፉ በ10 ነጥብ 1 በመቶ እድገት መጨመሩን ገልጸው፣ የ7 ነጥብ 9 በመቶ ሀገራዊ የኢኮኖሚ እድገትን ማሳካት እንደሚቻል ማሳያ ነው ብለዋል።

ባለፉት ጥቂት ዓመታት በተከታታይ የተተገበረው የኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ለዘርፉ መነቃቃት ትልቅ ሚና መጫወቱንም ገልጸዋል። በዘርፉ አዳዲስ ኢንቨስትመንትን በመሳብ ባለፉት አስር ወራት 129 ከፍተኛ ኢንዱስትሪዎች ወደ ስራ መግባታቸውን ነው ያብራሩት።በተለያዩ ምክንያቶች ስራ አቁመው የነበሩ ኢንዱስትሪዎች በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ ወደ ስራ እንዲገቡ እና የማምረት አቅማቸው እንዲያድግ መደረጉንም አቶ መላኩ አንስተዋል።

በተጨማሪም ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ የፋብሪካ ምርቶችን ለመተካት በተከናወኑ ተግባራት አበረታች ውጤቶች መመዝገቡ ተገልጿል፡፡ ይህ ውጤት በተሻለ መልኩ ቀጣይነት እንዲኖረው ለማስቻልም በ2017 በጀት ዓመት በኢንዱስትሪ ዘርፉ የ12 ነጥብ 8 በመቶ እድገት ለማስመዝገብ መታቀዱን አክለዋል።

Share this Post